Enedemer · እንደመር

እንደመር — ከማያውቁት ኢትዮጵያዊ ጋር በቪዲዮ ይጨዋወቱ

ነፃ የቪዲዮ ቻት። ያለ መተግበሪያ፣ ያለ ምዝገባ፣ ያለ VPN — ብራውዘርዎ ላይ ብቻ።

እንደመር ለአዋቂዎች ብቻ ነው — 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ።

እንደመር በዘፈቀደ ሁለት ሰዎችን አገናኝቶ በቀጥታ የቪዲዮ ውይይት የሚያስጀምር ነፃ አገልግሎት ነው። «START» ሲጫኑ ከሌላ ኢትዮጵያዊ ወይም ሀበሻ ጋር ፊት ለፊት ይገናኛሉ — አዲስ አበባ ያለ ተማሪ፣ ሪያድ ያለች ሠራተኛ፣ ወይም ዋሽንግተን ዲሲ ያለ ዲያስፖራ ሊሆን ይችላል። ውይይቱ ካላስደሰተዎት «NEXT» ይጫኑ — ወዲያውኑ ወደ ሌላ ሰው ይሸጋገራሉ።

ጨዋታ ይጀምሩ — ነፃ ነው፣ ምዝገባ የለም

በማንኛውም ስልክ ብራውዘር ላይ ይሰራል። ለ18+ ብቻ።

እንዴት ይሰራል?

  1. enedemer.com ይክፈቱ — Chrome ወይም ማንኛውም ብራውዘር በቂ ነው።
  2. START ይጫኑ እና ካሜራ ይፍቀዱ።
  3. ሲስተሙ ከሌላ ሰው ጋር ያገናኝዎታል — ይጨዋወቱ!
  4. ወደ ሌላ ሰው ለመሄድ NEXT፣ ለማቆም STOP ይጫኑ።

ምንም መተግበሪያ አይወርድም፣ ምንም አካውንት አይከፈትም፣ ስልክ ቁጥርም አይጠየቅም።

ዳታ ቆጣቢ ነው

ዳታ ውድ መሆኑን እናውቃለን። ስለዚህ የእንደመር ቪዲዮ ሆን ተብሎ የተገደበ ነው — አንድ ሰዓት ውይይት 125MB ገደማ ብቻ ይጠቀማል። አንድ ምሽት ሙሉ ጨዋታ በግምት 12 ብር አካባቢ ነው። ከምሽቱ 4 ሰዓት በኋላ ደግሞ የሌሊት ጉርሻ ዳታ ጋር ይገጥማል።

መቼ ብገባ ይሻላል?

ብዙ ሰው በመስመር ላይ ሲኖር ጨዋታው ይደራል። በየምሽቱ 2:30 የምሽት (8:30 PM) ላይ ብዙ ተጠቃሚ ይሰበሰባል — በዚያ ሰዓት ወረፋው በሰከንዶች ውስጥ ያገናኝዎታል። በሌላ ሰዓትም መግባት ይችላሉ፤ ትንሽ መጠበቅ ሊኖር ይችላል።

ደህንነትና ህግጋት

ስሙ ለምን «እንደመር» ሆነ?

«እንደመር» ማለት እስቲ አብረን እንደመር ማለት ነው — ሁላችንም በምናውቀው «መደመር» ቃል ላይ የተሰራ ቀልድ። አንድ ሰው ሲደመር አንድ ሰው — ውይይት ይሆናል። ያ ብቻ ነው መተግበሪያው።